ከአዲስ አበባ ውጪ ባሉ ብዙ ከተሞች ያየናቸው መሻሻሎች የተለያዩ አማራጮች እንዳሉን የሚያሳዩ ናቸው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር ) ገለፁ

You are currently viewing ከአዲስ አበባ ውጪ ባሉ ብዙ ከተሞች ያየናቸው መሻሻሎች የተለያዩ አማራጮች እንዳሉን የሚያሳዩ ናቸው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር ) ገለፁ

AMN ነሀሴ 10/2017 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር ) በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት አርባምንጭ በተፈጥሮ ስሪቷ ውብ መሆኗን ገልፀው በከተማዋ እየተካሄዱ ያሉ የልማት ሥራዎች በቅርቡ በጎበኘንበት ወቅት የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክትን ተመልክተናል ብለዋል፡፡

ይህ ሥራ በመጠነ ርዕዩ ግዙፍ በመሆኑ አርባምንጭ ታላላቅ ጉባኤዎችን እንድታስተናገድ ያስችላታል። ከዚህ ቀደም ከነበረን ምልከታ ሰፋ ብሎ የተከናወነው የኩልፎ ወንዝ ዳርቻ ልማት ለከተማዋ ልዩ መልኮች ተጨማሪ ገጽታ ፈጥሯልም ነው ያሉት።

ወደ አርባምንጭ ጫካ አዳዲስ የመግቢያ መንገዶች የተሠሩ ሲሆን ለተራሮቹ፣ ለውሃው እና ለከባቢው ደኖች መዳረሻ በር ሆነዋል። እነዚህና ሌሎች ከአዲስ አበባ ውጪ ባሉ ብዙ ከተሞች ያየናቸው መሻሻሎች የተለያዩ አማራጮች እንዳሉን የሚያሳዩ ያልተጠቀምንባቸውን አቅሞቻችንንም የሚገልጡ ናቸውም ብለዋል።

ይኽ እድገት በጋራ ጥረቶቻችን ታላላቅ ነገሮችን እንደምናሳካ የሚያመለክት ግልጽ ምልክት መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review