በሊቢያ ቤንጋዚ በተካሄደው የታዳጊ ወጣቶች አለም አቀፍ የብስክልት ውድድር የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሸነፈ

You are currently viewing በሊቢያ ቤንጋዚ በተካሄደው የታዳጊ ወጣቶች አለም አቀፍ የብስክልት ውድድር የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሸነፈ

AMN-ነሐሴ 10/2017 ዓ.ም

በሊቢያ ቤንጋዚ በተካሄደው የታዳጊ ወጣቶች አለም አቀፍ የብስክልት ውድድር የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በበላይነት አጠናቅቋል።

ብሄራዊ ቡድኑ ውድድሩ ላይ በቡድን እና በግል የተሳተፈ ሲሆን በሁለቱም ምድቦች በአንደኝነት ጨርሷል።

በዚሁ መሰረት በቡድን በተደረገው ውድድር ኢትዮጵያ፣ ሞሮኮ እና ግብፅ በተከታታይ ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ ሲይዙ በግል በተደረገው ውድድር ደግሞ ኢትዮጵያ፣ ሞሮኮ እና ኢትዮጵያ በመሆን በቅደም ተከተል ማጠናቀቃቸውን የብሄራዊ ቡድኑ ለኤ ኤም ኤን በላከው መረጃ ገልጿል ።

ውጤቱን መሰረት በማድረግም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የተዘጋጁትን ሁለቱንም የወርቅ ሽልማቶች እና የገንዘብ ማበረታቻ

መውሰድ ችሏል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review