የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የዩክሬኑ አቻቸዉ ቮሎድሚር ዘለንስኪ የሩሲያና ዩክሬንን ጦርነት ለማስቆም በሚቀጥለዉ ሰኞ በዋሽንግተን በአካል ተገናኝተዉ ሊመክሩ መሆኑ ተነግሯል፡፡
ዶናልድ ትራምፕ ከዘለንስኪ ጋር የሚያደርጉት ውይይት ዉጤታማ ከሆነ በቀጣይ ከሩሲያ አቻቸዉ ቭላድሚር ከፑቲን ጋር ሊመክሩ እንደሚችሉ በትሩዝ ማህበራዊ የትስስር ገጻቸዉ ገልጸዋል፡፡
በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል ያለውን አሰቃቂ ጦርነት ለማስቆም ተመራጩ መንገድ በቀጥታ ወደ የሰላም ስምምነት መሄድ ነው ያሉት ትራምፕ፣ ይህም ጦርነቱን የሚያስቆም እንጂ ተራ የተኩስ አቁም ስምምነት አይደለም” ማለታቸዉን አርቲ ዘግቧል፡፡
በአስማረ መኮንን