የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በፈታኝ የአመራር ክህሎት ያሰለጠናቸዉን ስትራቴጅክና ከፍተኛ የፖሊስ አመራሮችን በአዋሽ ሰባት ማሰልጠኛ ማዕከል አስመረቀ

You are currently viewing የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በፈታኝ የአመራር ክህሎት ያሰለጠናቸዉን ስትራቴጅክና ከፍተኛ የፖሊስ አመራሮችን በአዋሽ ሰባት ማሰልጠኛ ማዕከል አስመረቀ

AMN ነሃሴ 10/2017

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በፈታኝ የአመራር ክህሎት (Leadership challenge) ያሰለጠናቸዉን የፌደራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ ስትራቴጅክና ከፍተኛ የፖሊስ አመራሮችን በአዋሽ ሰባት ማሰልጠኛ ማዕከል አስመርቋል፡፡

በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የፖሊስ ሠራዊቱ የሚሰጠውን ተልዕኮ ተሸክሞ ሊሄድ የሚችል የአመራር አቅም ለመፍጠር ፈታኝ የአመራር ክህሎት (Leadership challenge) ስልጠና በተግባር ውጤት እያመጣ መሆኑን ተናረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፖሊስ ፕሮፌሽናል ሆኖ እንዲገነባ፤ ያደገና የበቃ አመራር እንዲኖረው መንግስት ለሪፎርሙ በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት መሠረት ዛሬ ላይ የፖሊስ የማድረግ አቅም እያደገ አገልግሎቱ እየዘመነ ለሀገርም ለአካባቢው ቀጠናም ሞዴል እየሆነ የመጣ ተቋም መሆኑን ገልፀዋል ።

በየደረጃው የሚገኘውን የሠራዊቱን የመምራት፤ የማብቃት እንዲሁም የሚሰጠውን የትኛውንም ተልዕኮዎች በብቃት የመወጣት አቅሙን ለማሳደግ በየጊዜው በሚካሄዱ ጥናቶች የሚታዩ የአመራር ክፍተቶችን በመለየት የተለያዩ የአመራሩን አቅም የሚገነቡ ስልጠናዎች እየተሰጡ መሆኑን ተናግረዋል።

ስትራቴጅክና ከፍተኛ የፖሊስ አመራሮች ያገኙትን ስልጠና ወደ ታች በማውረድ ሠራዊቱን በማብቃት ሀገሩን የሚወድና በፅናት የሚያገለግል የፖሊስ ኃይል እንዲፈጠር መስራት እንደሚጠበቅባቸውም አሳስበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩንቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መስፍን አበበ በበኩላቸው ስትራቴጅክና ከፍተኛ አመራሮች የLeadership challenge ስልጠናውን በከፍተኛ ፖሊሳዊ ዲስፕሊን፣ በቁርጠኝነትና በስኬት በማጠናቀቅ ማንኛውንም ፈተና በብቃት የሚወጣ፤ ተልዕኮውንም በስኬት የሚፈፅም ከፍተኛ የአመራር አቅም መፈጠሩን መናገራቸዉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በላከዉ መረጃ አስታዉቋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review