የ2025 የዳይመንድ ሊግ የ12ኛ ከተማ ውድድር ዛሬ በፖላንድ ሲላሲያ እየተካሄደ ነው፡፡ ተጠባቂ የነበረውን የ1 ሺ 500 ሜትር ሴቶች ሩጫ አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ አሸንፋለች፡፡
ጉዳፍ አብዛኛውን ዙር ተነጥላ በመውጣት ዋነኛ ተፎካካሪዋን ቢትሪ ቺቤትን በማሸነፍ በአንደኝነት አጠናቃለች፡፡ ውድድሩን ለማሸነፍ ግምት ካገኙ አትሌቶች መካከል የነበረችው ቢትሪስ ቺቤት ሁለተኛ ደረጃን አግኝታለች፡፡
ፍሬወይኒ ኃይሉ አምስተኛ እንዲሁም ብርቄ ኃየሎም ሰባተኛ ደረጃን ይዘው ውድድራቸውን አጠናቀዋል፡፡
በታምራት አበራ