ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ወላይታ ሶዶ አረንጓዴ ኢትዮጵያን የመገንባት ጽኑ አቋም ምስክር መሆኗን ገልጸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ወላይታ ሶዶ አረንጓዴ ኢትዮጵያን የመገንባት ጽኑ አቋማችን ምስክር ናት ብለዋል፡፡
ከአርባምንጭ እስከ ወላይታ ስንጓዝ የአረንጓዴ ልማት ሥራችን ውጤት እንዲሁም አስደናቂ የፍራፍሬ እርሻ ልማት መስክ ተመልክተናል።
እነዚህ ጥረቶች የመልከዓ ምድሩን ልምላሜ ከመመለስ ባሻገር የአኗኗር ዘይቤንም የማሸጋገር ሥራዎች ናቸው።
በጠንካራ የሥራ ባሕሉ እና ኅብረቱ የሚታወቀው የወላይታ ሕዝብ በዚህ የለውጥ ሂደት ውስጥ ጠንካራ ሚና መወጣቱን ቀጥሏል ሲሉ ገልጸዋል፡፡