የባንኩ አመራርና ሰራተኞች በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በተለያዩ አካባቢዎች የተሳተፉ ሲሆን፣ በዛሬው እለትም በሸገር ከተማ ኮዬ ክፍለ ከተማ፥ ወዴሳ ወረዳ የችግኝ ተከላ አካሂደዋል።
በመርሃ ግብሩም የሸገር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር)፣ የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ ነዋይ መገርሳ፣ እንዲሁም የባንኩ ሰራተኞች እና የሸገር ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
የሸገር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር) ባንኩ የፋይንናስ ተደራሽነትን ለማሳደግ ከሚያከናውናቸው ተግባራትን ጎን ለጎን በዛሬው እለት ያካሄደው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የሸገር ከተማን ገጽታ ለመቀየር የሚያግዝ መሆኑን ተናግረዋል።
የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ ንዋይ መገርሳ በበኩላቸው፥ ባንኩ በባንክ እና ማይከሮፋይናንስ ጥምር አገልግሎት ሚሊዮኖችን ተጠቃሚ ከማድረግ ባሻገር ማህበራዊ ሃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን ተናግረዋል።