ማንችስተር ሲቲ አዲሱን የውድድር ዓመት በድል ጀምሯል ። ከሜዳው ውጪ ወልቭስን የገጠመው ሲቲ 4ለ0 ማሸነፍ ችሏል።
ለሲቲ ግቦቹን ኧርሊንግ ሃላንድ ሁለት ግብ ሲያስቆጥር ፣ አዲስ ፈራሚዎቹ ቲጃኒ ራይንደርስ እና ረያን ቸርኪ ተጨማሪ ግቦቹን ከመረብ አሳርፈዋል።
በርካቶች ከወንጫ ፉክክሩ ያራቁት ማንችስተር ሲቲ ጠንካራ አጀማመር አሳይቷል።
ወልቭስ ጨዋታው ከመጀመሩ በፊት ሃምሌ ወር ላይ ከወንድሙ ጋር ሕይወቱን ያጣው የቀድሞ ተጫዋቻቸው ዲያጎ ጆታን አስበዋል።
በዝውውሩ ወሳኝ ተጫዋቾቹን ያጣው ወልቭስ ዘንድሮም አስቸጋሪ የውድድር ዓመት ሊያሳልፍ እንደሚችል አሳይቷል።
በሸዋንግዛው ግርማ