የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአንጋፋው አርቲስት ደበበ እሸቱ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል፡፡
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ በኢትዮጵያ የቲያትር ጥበብ ውስጥ ጉልህ አሻራ ባሳረፈው አንጋፋው አርቲስት ደበበ እሸቱ ህልፈት የተሰማኝን ጥልቅ ሃዘን እየገለጽኩ፤ ለወዳጅ ዘመዶቹ እና ለአድናቂዎቹ መጽናናትን እመኛለሁ ብለዋል።
ፈጣሪ ነብሱን በአጸደ ገነት ያኖረው ዘንድም ተመኝተዋል።