ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንጋፋው አርቲስ ደበበ እሸቱ ሕልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገልጸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ በኢትዮጵያ ዘመናዊ የኪነ ጥበብ ታሪክ ታላቅ ዐሻራ ያሳረፈው አርቲስት ደበበ እሸቱ በማረፉ ጥልቅ ኀዘን ተሰምቶኛል ብለዋል።
ደበበ እሸቱ ለዘመናዊት ኢትዮጵያ ቴአትርና ፊልም ዕድገት ፋና ወጊ ከሆኑት ልሂቃን አንዱ ነው ሲሉም ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ የጀመረችውን የለውጥ ጉዞ በጽናት እንድታሳካ በኪነ ጥበብ ተሰጥዖው ያበረከተውን ሚና ዘወትር ስናስታውሰው እንኖራለን በማለትም አክለዋል።
ፈጣሪ ነፍሱን ያሳርፍ ዘንድም ምኞታቸውን ገልጸዋል።