የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ዴር ሌየን፣ ዜለንስኪ ከትራምፕ ጋር በሚያደርጉት ስብሰባ ከአውሮፓ መሪዎች ጋር እንደሚሳተፉ አስታውቀዋል።
ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከአላስካው ውይይት በኋላ፣ በዩክሬን የያዙትን አፋጣኝ የተኩስ አቁም ስምምነት አቋም ውድቅ አድርገዋል።
የሩሲያ-ዩክሬንን ጦርነት ለማስቆም የተሻለው መንገድ በሀገራቱ መካከል ቀጥታ የሰላም ስምምነት ማድረግ ነው ብለዋል፡፡
ከአላስካ ወደ ዋሽንግተን ሲመለሱ፣ ዘሌንስኪን እና የአውሮፓ መሪዎችን እንደሚያነጋግሩ የገለጹት ትራምፕ፣ የተኩስ አቁም ስምምነቶች ብዙ ጊዜ አይቆዩም ሲሉ መግለፃቸውን አር ቲ ኢ ዘግቧል።
ይሁን እንጂ በአካሄዱ ለውጥ ያላመኑት ፕሬዚዳንት ዜሌንስኪ፣ ትራምፕ የመረጡት መንገድ “ሁኔታውን ያወሳስበዋል” በማለት ገልጸዋል።
በብርሃኑ ወርቅነህ