የተካሔደው ምርጫ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መልኩ መጠናቀቁን የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ገለፀ

You are currently viewing የተካሔደው ምርጫ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መልኩ መጠናቀቁን የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ገለፀ

AMN – ነሐሴ 11/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ዛሬ በአራት ዘርፎች ያደረገው ምርጫ ሰላማዊ በሆኑ መልኩ መጠናቀቁን አስታወቀ።

ከፍተኛ ምክር ቤቱ የ2017 ምርጫ አስፈፃሚ ቦርድ በዛሬው ቀን ነሐሴ 11/2017 ዓ.ም በ334 የምርጫ ጣቢያዎች በአራት ዘርፎች ማለትም በጠዋቱ ክፍለ ጊዜ የወጣቶችና የምሁራን፤ በከሠዓቱ ክፍለ ጊዜ ደግሞ የሴቶችና የሠራተኛው ማህበረሰብ ዘርፎች ሲካሄድ የነበረው የሕዝበ ሙስሊሙ ምርጫ ፍፁም ሠላማዊ በሆነ መልኩ ተጠናቋል ሲል ገልጿል::

ምክር ቤቱ ይሄን እድል ለሕዝበ ሙስሊሙ ለሠጠው መንግስትም በሕዝባችን ስም ከልብ እናመሰግናለን ማለቱን ኢዜአ ዘግቧል።

በተጨማሪም ነሐሴ 9 ቀን 2017 በነበረው የዑለሞች ምርጫና በዛሬው ቀን ነሐሴ 11 የተካሄደው የአራት ዘርፎች ምርጫ፤ ፍፁም ሠላማዊ በሆነ መልኩ እንዲከናወን የአዲስ አበባ ሠላምና ፀጥታ ቢሮና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እንዲሁም ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ላደረጉት ድጋፍ በመላው ሕዝበ ሙስሊም ስም ላቅ ያለ ምስጋና ለማቅረብ እንወዳለን ብሏል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review