የአርቲስት ደበበ እሸቱ ስርዓተ ቀብር በነገው እለት በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንደሚፈፀም ተገለጸ

You are currently viewing የአርቲስት ደበበ እሸቱ ስርዓተ ቀብር በነገው እለት በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንደሚፈፀም ተገለጸ

AMN – ነሐሴ 12/2017 ዓ.ም

በትላንትናው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው፣ የሬዲዮ እና የቴሌቪዥን ድራማና ፊልሞች ተዋናይ፣ ጋዜጠኛ እንዲሁም የመድረክ መሪ የአንጋፋው አርቲስት ደበበ እሸቱ ስርዓተ ቀብር በነገው እለት በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በስምንት ሰዓት እንደሚፈፀም ተገልጿል።

ከቀብር ስነ-ስርዓቱ አስቀድሞ ለበርካታ ዓመታት ባገለገለበት ብሔራዊ ቲያትር

ከቀኑ አምስት ሰዓት የአስክሬን ሽኝት ስነ-ስርዓት እንደሚደረግለት ተጠቁሟል።

አርቲስት ደበበ እሸቱ በርካታ የጥበብ ስራዎችን ለጥበቡ ቤተሰብ ያበረከተ ሲሆን፣ ተዋንያንን ለማስተማር የሚያግዝ መፅሃፍም ፅፏል።

በመቅደስ ደምስ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review