የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት “ዛሬ የ90 ቀን የሁለት ወር ሥራ አፈፃፀም ገምግመናል”ብለዋል።
የአገልግሎት አሰጣጥ ማዘመን እና የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ የሚቀርቡ ግብአቶች አቅርቦትን ፣ የገበያ ማረጋጋት ፣የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ ፣ የፕሮጀክቶች ግንባታ፣ የገቢ አፍፃፀም እና ለኮንፍረንስ የቱሪዝምን ምቹ ሁኔታ መፍጠር በትኩረት ገምግመናልም ብለዋል።
በዚህም የሁለቱ ወር ስራ አፍፃፀም ውጤታማ እንደነበረም በርካታ ማሳያዎች ቀርበዋል ያሉትፐከንቲባ አዳነች በተለይ ከኑሮ ውድነት ጋር ተያይዞ ምርቶች በስፋት ወደ ከተማው መግባታቸው ፣ የገቢ አፈፃፀም፣ የክረምት በጐ ፍቃድ አገልግሎት፣ የስራ እድል ፈጠራ እና የፕሮጀክቶች አፈፃፀም የተሻሉ እንደነበራቸውም ጠቅሰዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ መሻሻል የሚገባቸው እና በክፍታት የታዩትን በፍጥነት እንዲታረም አቅጣጫ ማስቀመጣቸውን ባሰፈሩት መልዕክት ጠቁመዋል።
ከንቲባ አዳነች አክለውም ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ የሚከናወኑት 2ተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ እንዲሁም የካሪቢያን መሪዎች ታላላቅ ስብስባ እና ጉባኤን በፍጹም ፀጥታ፣ በትሁት ኢትዮጵያዊ መስተንግዶ ተቀብለን ለማስተናገድ ከወትሮው የተለያ ርብርብ እንድናደርግ ፤ ሁሉም የከተማው አመራር በትኩረት እንዲሰራ ተግባብተናል ብለዋል።
ማህበረሰቡም ለእንግዶቹ ኢትዮጵያዊ ጨዋነትን በተግባር እንዲያሳይ ከንቲባ አዳነች ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።