የአዲስ አበባን ተምሳሌትነት እና የኢትዮጵያን የከፍታ ጉዞ ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል ተግባቦት መፈጠሩን በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስታወቀ

You are currently viewing የአዲስ አበባን ተምሳሌትነት እና የኢትዮጵያን የከፍታ ጉዞ ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል ተግባቦት መፈጠሩን በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስታወቀ

AMN ነሃሴ 13/2017

የአዲስ አበባን ተምሳሌትነት እና የኢትዮጵያን የከፍታ ጉዞ ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል በቀጣይም የፓርቲዉን አሻጋሪ እሳቤዎች በቁርጠኝነት ለመፈፀም እንዲሁም ለማስፈፀም ተግባቦት መፈጠሩን በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስታዉቋል፡፡

በአዲስ አበባ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች የአስተሳሰብና የተግባር አንድነትን በማጠናከር እንደ ሀገር ከነበርንበት የቁልቁለት ጉዞ ለማንሰራራት፣ ባለፉት ሰባት አመታት በተከናወኑ ተግባራት የተገኙ ስኬቶችን አልቆ ለማስቀጠል ፣ ጉለቶችንም በማረም ለታለመለት ሁለንተናዊ ስኬት ለመድረስ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ለሶስት ቀናት ሲያካሄዱት የነበረውን ውይይት በተሻለ ተነሳሽነት ለላቀ ውጤት ለመትጋት ተግባቦት ላይ በመድረስ መጠናቀቁን በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስታዉቋል፡፡

ሀገራዊ ለውጡ እውን ሲሆን ከተማዋ እንዲሁም በሃገሪቱ የነበሩበት ነባራዊ ሁኔታ ፣ የነበሩ ውስብስብ ችግሮችን በመሻገር ታሪካዊ ስብራቶችን ለመጠገን የተወሰዱ እርምጃዎች ፣ የገጠሙ ተግዳሮቶች እና በፈተናዎች ውስጥ የተመዘገቡ አንፀባራቂ ድሎች በውይይቱ መዳሰሱን ጽ/ቤቱ ገልጿል፡፡

ጠንካራ ፓርቲ በመገንባት የመንግስትን የመፈፀም አቅም ለማሳደግ የተያዘው አቅጣጫ ተግባራዊ እየተደረገ በመሆኑ ተነሳሽነትን ከፍ የሚያደርጉ ስኬቶች በየዘርፉ መመዝገባቸውም በውይይቱ ተመላክቷል።

ለሶስት ቀናት ሲካሄድ በቆየው ውይይትም የአዲስ አበባን ተምሳሌትነት እና የኢትዮጵያን የከፍታ ጉዞ ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል በቀጣይም የፓርቲዉን አሻጋሪ እሳቤዎች በቁርጠኝነት ለመፈፀም እንዲሁም ለማስፈፀም ተግባቦት መፈጠሩን በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስታዉቋል፡፡

ሁለንተናዊ ብልፅግናን የማረጋገጥ ራዕይ አሳታፊ እና አካታች ነው። አመራሩም ፣ አባላትም ፣ ሁሉም ዜጋ በየተሰማራበት ታሪካዊ ኃላፊነቱን በመወጣት አሻራውን ሲያሳርፍ የሀገሪቱን ልዕልና የማረጋገጥ ጉዞ ይበልጥ ይፋጠናል።

መንግስት በሰላም ስራዎች ላይ የጀመራቸውን ስራዎች አጠናክሮ በመቀጠል ፣ የዜጎችን ሰላም ለማረጋገጥ በልዩ ትኩረት እየሰራ ሲሆን ፣ በየጊዜው የሚደረጉ መሰል ውይይቶች ደግሞ ወቅታዊ ፣ ሀገራዊ ፣ ቀጠናዊና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች ላይ ተቀራራቢ ግንዛቤ በማስያዝ ጭምር ፣ በፓርቲዉ ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ግልፅነት ፈጥሮ ተልዕኮን በተቀናጀ አግባብ ለመፈፀም የጎላ አበርክቶ እንደሚኖረዉ ገልጿል፡፡

በየደረጃው ያለው አመራርም በአገልግሎት አሰጣጡ ፣ ሌብነት እና ብልሹ አሰራርን በመታገል ፣ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ እና የልማት አርበኛ በመሆን ለሁለንተናዊ ብልፅግና ስኬት ለመትጋት ተነሳሽነት በመፍጠር ለተሻለ ስኬት እንደሚሰሩ ማንሳቱን ጽ/ቤቱ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በላከዉ መረጃ አስታዉቋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review