ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በድሬዳዋ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን ይጎበኛሉ

You are currently viewing ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በድሬዳዋ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን ይጎበኛሉ
  • Post category:ልማት

AMN- ነሐሴ 13/2017 ዓ.ም

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ጨምሮ በከተማዋ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን የስራ ሂደት ለመመልከት ድሬዳዋ ገብተዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ በትንሿ ኢትዮጵያ፣ በበረሀዋ ገነት፣ በጉራማይሌዋ የፍቅር ከተማ ድሬ ገብተናል ብለዋል፡፡

በድሬዳዋ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደማቅ አቀባበል ላደረጉልን ለድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ፣ ለከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች፣ ለሀገር ሽማግሌዎች እና ለከተማው ህዝብ ላቅ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ ሲሉም ገልጸዋል፡፡

በቆይታችን የኮሪደር ልማት ስራዎችን ጨምሮ በከተማዋ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን የስራ ሂደት የምንመለከት ይሆናልም ብለዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review