ዴቪድ ሀምፕሰን በእንግሊዝ ያልተፈታ ሚስጥር ሆኖ ለ11 ዓመታት ዘልቋል፡፡
በእንግሊዝ ስዋንሲ ከተማ መስቀለኛ ስፍራ ላይ በመቆም የትራፊክ ፍሰት ሲያጨናንቅ የኖረው ዴቪድ፣ ይህን ለምን እንደሚያደርግ ግን እስካሁን ድረስ አልታወቀም፡፡
ዴቪድ ፖሊስ ስፍራው መጥቶ እስኪያስረው ድረስ እንደ ግዑዝ ፍጡር ፈፅሞ አይንቀሳቀስም፡፡
ዴቪድ ከማንም ጋር አይነጋገርም፤ ፖሊሶች ሲያጣድፉትም አያወራም፡፡
ይህን እኩይ ተግባር ለምን እንደሚፈፅም ማብራሪያ ከሚሰጥ ለወራት በእስር ቤት መክረምን ይመርጣል፡፡
በስዋንሲ ጎዳና እንደተለመደው መሀል መንገድ ላይ ቆሞ የትራፊክ ፍሰት ሲያስተጓጉል ተይዞ ለመጨረሻ ጊዜ በተያዘው የፈረንጆቹ 2025 ሰኔ 19 ላይ ፍርድ ቤት ቀርቧል፡፡
በሂደቱ ከፖሊሶች፣ ከዳኞች፣ ከአቃቤ ህጎች እና ከሀኪሞች ጋር ለመነጋገር አልፈቀደም፡፡
ዝምታ መፍትሄ እንደማይሆን ቢነገረውም፣ እንደ ሀውልት ከፊታቸው ሆኖ ዝም ከማለት ውጭ ምንም አልተነፈሰም፡፡
ይህ እንግዳ ነገር የሆነበት ፍርድ ቤቱ፣ ዴቪድ ምናልባት በተፈጥሮ መናገር የማይችል አሊያም መናገር እየቻለ ነገር ግን መናገር ጠልቶ ከሆነም ለዓመታት ያህል የምርመራ ሥራ አካሂዷል።
ጥናቱ ዴቪድ መናገር እየቻለ ነገር ግን መናገር እንደማይፈልግ አረጋግጧል።
ይህ መረጃ የተገኘው ከዴቪድ ጋር የቀረበ ወዳጅነት ከነበራቸው የእስረኞች ኃላፊዎች ነው።
ዝምተኛው ዴቪድ በጥሩ ንግግር ይጫወት ነበር ብለዋል።
ግለሰቡ ምንም አይነት የጤና እክል አጋጥሞት እንደማያውቅም በጤና ተቋማት የተደረገ ምርመራ አመልክቷል።
ዴቪድ ሀምፕሰን በተመሳሳይ ድርጊት ውስጥ 11 ዓመታትን በአነጋጋሪነቱ መዝለቁን የኦዲቲ ሴንትራል ዘገባ ያሳያል።
በእያንዳንዱ ወንጀል ታስሮ ከተለቀቀ በኋላ የሚገኘው እዚያው የስዋንሲ ጎዳና ላይ የተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴ ሲገድብ ነው።
በማሬ ቃጦ