6ኛው ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦሌ ክፍለ ከተማ በይፋ ተከፍቷል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚወሉ መሬቶችን በጨረታ አወዳድሮ ያስተላልፋል፡፡
ቢሮው በ6ኛው ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ በ7 ክፍለ ከተሞች 132 ፕሎቶች ወይም ቦታዎች መዘጋጀታቸውን አስታውቋል፡፡
በመክፈቻ መርሀ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ መኮንን ያኢ፣ 5 ሺህ 215 ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በበይነ መረብ ገዝተዋል ብለዋል፡፡
በዚህ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታም 42 ሺህ ካሬ ሜትር መሬት ለጨረታ መቅረቡንም ኃላፊው ተናግረዋል፡፡
ከጨረታ ሰነድ ሽያጩም 11.9 ሚሊየን ብር ገቢ መገኘቱን ኃላፊው አብራርተዋል፡፡
6ኛው ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ለ 3 ቀናት እንደሚቆይ የተናገሩት የቢሮው ኃላፊ፣ በዛሬው እለት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ጨረታ የወጣባቸው 45 ቦታዎች ጊዜያዊ ውጤት ይፋ እንደሚደረግም ተናግረዋል፡፡
በ 2018 በጀት ዓመት የመሬት ሊዝ ጨረታ በተከታታይ እንደሚካሄድ የተናገሩት ኃላፊው፣ ከመሬት ሊዝ ሽያጭ 18 ቢሊየን ብር ለማስገባት እቅድ መያዙንም ተናግረዋል፡፡
በቴዎድሮስ ይሳ