የእንግሊዝ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋቾች ማህበር የ2024/25 የውድድር ዓመት ኮከቦችን ሸልሟል ።
በአዋቂዎች የዓመቱ ምርጥ በሚል ሞሃመድ ሳላህ ተመርጧል ። ሽልማቱን ለሦስት ጊዜ ያሸነፈ ብቸኛው ተጫዋችም ሆኗል።
የ33 ዓመቱ ግብፃዊ በውድድር ዓመቱ በሊጉ ባደረጋቸው 38 ጨዋታ 29 ግብ አስቆጥሮ 18 ወደ ግብነት የተቀየሩ ኳሶችን ማቀበል ችሏል ።
የጎላ ተፅዕኖም ሊቨርፑልን የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን አድርጓል ።
በሴቶች የአርሰናሏ ስፔናዊ አጥቂ ማሪኦና ካልዴንቴ መመረጥ ችላለች ።
በወጣቶች ዘርፍ ከአስቶንቪላ ጋር ድንቅ የውድድር ዓመት ያሳለፈው ሞርጋን ሮጀርስ ተመርጧል ።
በሴቶች ክብረወሰን አሻሽላ ከሊቨርፑል አርሰናልን የተቀላቀለችው ኦሊቪያ ስሚዝ ተሸልማለች ።
የቀድሞ የቼልሲ አሰልጣኝ ኤማ ሃይስ እና ለበርካታ ዓመታት የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድንን የመራው ጋሬት ሳውዝጌት በስፖርቱ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ልዩ ተሸላሚ ሆነዋል ።
የእንግሊዝ ፕሮፌሽናል እግርኳስ ተጫዋቾች ማህበር ያዘጋጀው ሽልማት የዓመቱ ምርጥ ቡድንን መምረጥ ጨምሮ በበርካታ ዘርፎች ሽልማት አበርክቷል ።
የአመቱ ምርጥ ቡድን ውስጥ ሊቨርፑል አራት አርሰናል ሦስት ተጫዋቾችን አስመርጠዋል ።
በሸዋንግዛው ግርማ