በመላው ኢትዮጵያ ምክር ቤቶችን የማቋቋም እና መሪዎችን የመምረጥ ሥራ እንደሚከናወን ተገለጸ

You are currently viewing በመላው ኢትዮጵያ ምክር ቤቶችን የማቋቋም እና መሪዎችን የመምረጥ ሥራ እንደሚከናወን ተገለጸ

AMN – ነሃሴ 14/2017 ዓ.ም

በመላው ኢትዮጵያ ምክር ቤቶችን የማቋቋም እና መሪዎችን የመምረጥ ሥራ ከነሐሴ 14/ 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 7 ቀናት እንደሚከናወን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ2017 ምርጫ አስፈጻሚ ቦርድ አስታወቀ፡፡

ቦርዱ የመጀመሪያው ዙር በመስጂድ ደረጃ በተለያዩ ዘርፎች የተካሄደው ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ በስኬት መጠናቀቁ አስታውቋል፡፡ ለዚህ ስኬትም ህዝበ ሙስሊሙን አመስግኗል፡፡

በቀጣይም በየደረጃው ምክር ቤቶችን የማቋቋም እና መሪዎችን የመምረጥ ሥራ የሚከናወን መሆኑን ያስታወቀው ቦርዱ፣ በተያዘው መርሃ ግብር መሠረትም ከነሐሴ 14 /2017 ጀምሮ ዓ.ም ባለው የአንድ ሣምንት ጊዜ ውስጥ እንደየ አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ የወረዳ ምክር ቤቶች ይቋቋማሉ፡፡

በመሆኑም ከየመስጂዱ የተመረጡት ተመራጮች ወደየ ወረዳቸው በመሄድ ለወረዳ ምክር ቤት ስለሚመራረጡ ህዝበ ሙስሊሙም ይህንን መርሃ ግብር ተረድቶ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል፡፡

በሌላ በኩል ተመራጮችም በወረዳ ደረጃ ማሟላት የሚገባችውን መስፈርቶች በማሟላት ሹራን መሠረት ባደረገ በኢስላማዊ ሥነ-ምግባር በተጠቀሱት ቀናት በየወረዳው ለምርጫ በተለያዩ መስጂዶች በመገኘት ምክር ቤቱን እንዲያቋቁሙ ሲል የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላ ምክር ቤት ምርጫ አስፈጻሚ ቦርድ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

በአንዋር አህመድ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review