ህዝቡን መሠረት ያደረጉ የሰላምና የፀጥታ ተግባራት በመከናወናቸው የመዲናዋን ሰላም ለማረጋገጥ እንደተቻለ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ገለጸ

You are currently viewing ህዝቡን መሠረት ያደረጉ የሰላምና የፀጥታ ተግባራት በመከናወናቸው የመዲናዋን ሰላም ለማረጋገጥ እንደተቻለ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ገለጸ

AMN – ነሃሴ 14/2017 ዓ.ም

ህዝቡን መሠረት ያደረጉ የሰላምና የፀጥታ ተግባራት በመከናወናቸው የመዲናዋን ሰላም ለማረጋገጥ እንደተቻለ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀለፊ ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከተማ አቀፍ አምስተኛ ኮርስ እጩ የሰላም ሰራዊት አባላት ስልጠና መስጠት ጀምሯል።

በ2017 ዓ.ም በመዲናዋ ትላልቅ ዓለም አቀፍ ሁነቶች እንዲሁም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች የተገኙባቸው ሐይማኖታዊና ባህላዊ በዓላት ሰላማቸው በተጠበቀ ሁኔታ በስኬት መካሄዳቸውን የጠቅሱት ሀላፊዋ፣ ለዚህም በየአካባቢው የተደራጁ የሰላም ሰራዊት አባላት ሚና ከፍተኛ ሚና እንደነበራቸው ተናግረዋል።

ይህን አደረጃጀት ለማጠናከር በ2018 ዓ.ም በርካታ ተግባራት እንደሚከናወኑ እና አሁን መሠጠት የተጀመረው ስልጠናም አደረጃጀቱን የማጠናከር አንዱ የተግባር አካል መሆኑን ተናገረዋል።

ስልጠናው የንድፈ ሃሳብ እና ወታደራዊ የመስክ ስልጠና የያዘ ሲሆን፣ ከ11ሺህ በላይ አዲስ ምልምል ሰልጣኞች በ11ዱም ወረዳዎች ስልጠናውን ለተከታታይ 15 ቀናት እንደሚወስዱ ተመላክቷል፡፡

በታምሩ ደምሴ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review