የመደመር መንግስት መጽሃፍ ለአፍሪካ መንግስታት ጭምር ፈር ቀዳጅ እንደሚሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ

You are currently viewing የመደመር መንግስት መጽሃፍ ለአፍሪካ መንግስታት ጭምር ፈር ቀዳጅ እንደሚሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ

AMN – ነሐሴ 14/2017 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቅርቡ የመደመር መንግስት በሚል ርእስ ያሳተሙት መጽሃፍ የሀሳብ ጽንሰት፣ የረቂቅ ዝግጅትና ውልደት እንዴት እንደነበር በዝርዝር አስተድተዋል፡፡

የመደመር መንግስት መጽሃፍ ሀሳቡ በተለያየ ደረጃ ሊተገበር የሚችል እንደሆነ ያብራሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በግል፣ በቤተሰብ፣ በሰፈር፣ በቡድን፣ በሚሰራባቸው መስሪያ ቤቶች፣ ሁሉ ሊተገብረው የሚችል ሀሳብ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ መደመር በእኔም ህይወት ረዘም ላለ ጊዜ የነበረ፣ የተለማመድኩት፣ በሰራሁባቸው መስሪያ ቤቶች ሁሉ ፍሬ ያፈራሁበት ሀሳብ ነው ብለዋል፡፡

ነገር ግን ይህ ሀሳብ ወደ መንግስት ሀሳብነት ያደገው በሂደት ነው ብለዋል፡፡ ከግል አልፎ ወደ የመንግስት አቋም ለመሆን በርከት ያለ ጊዜ ወስዶበታል ብለዋል፡፡

ሀሳቡ በስልጠና፣ በሃሳብ ልውውጦች፣ ሰነዶችን በማገላበጥና ተጨማሪ ምልከታዎች፣ በማድረግ በሂደት እያደገ የመጣና ወደ መድሃፍነት የተለወጠ፣በዚህም ሀሳቡን የወል ለማድረግ በርካቶች የሚቀበሉት እና የሚሰሩበት እና የሚጠቀሙበት ሀሳብ ነው ብለዋል፡፡

ይህ መጽሃፍ በውስጡ ታሪክን የሚዳስስ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ወደኋላ መለስ ብሎ ለራሱ ህልም የሚፈይድ ታሪኮችን በመጠኑ እንደሚዳስስም ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም መጽሃፉ ወደ ፊት መራመድን ያለመ፣ ዓለም ወዴት እያመራች እንደሆነ እና እኛ ምን ማድረግ እንዳለብን ይተነትናል ብለዋል፡፡

ከሁሉም በላይ የመደመር መንግስት መጽሃፍን ጠቃሚ እና አስፈላጊ የሚያደርገው ከተጨባጭ ልምድ የተነሳ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕምድ (ዶ/ር) አብራርተዋል፡፡

መጽሃፉ ከንድፍ ሀሳብ ብቻ የተነሳ ሳይሆን በሂደት ከተገኙ ልምዶች እየዳበረ፣ በሀሳብ እየጎለበተ፣ እየታረቀ እና ፍሬያማ በሆኑ ሀሳቦች ዳብሮ የወጣ መጽሃፍ ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

መጽሃፉ፣ ለብዙዎች ፈር ቀዳጅና መንግስታም ምን አስበው እንዴት እንደሚተገብሩ ለህዝባቸው እና ለታሪክ የሚተውት ሰነድ እንደሚሆን እተማመናለሁ ብለዋል፡፡

በአስማረ መኮንን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review