አርሰናል ኤቤሬቼ ኤዜን ለማስፈረም ተስማማ

You are currently viewing አርሰናል ኤቤሬቼ ኤዜን ለማስፈረም ተስማማ

AMN – ነሃሴ 14/2017 ዓ.ም

አርሰናል ኤቤሬቼ ኤዜን ለማስፈረም ከክሪስታል ፓላስ ጋር ተስማምቷል።

መድፈኞቹ ለ27 ዓመቱ እንግሊዛዊ እስከ 68 ሚሊየን ፓውንድ ለመክፈል ከስምምነት መድረሳቸውን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።

አርሰናል ቀድሞም ኤዜን የማስፈረም ፍላጎት ቢያሳይም ባለፉት ቀናት ተቀዛቅዞ ነበር። የካይ ሀቨርትዝ ጉዳት ግን ወደ ገበያው እንዲወጣ አስገድዶታል።

ቶተንሃም ሆትስፐርስን ለመቀላቀል ከጫፍ ደርሶ የነበረው ኤዜ ሃሳቡን ቀይሮ ወደ ኤምሬትስ ለማቅናት ተቃርቧል።

በአርሰናል አካዳሚ ሰልጥኖ 13 ዓመት ሲሞላው ከክለቡ የተሰናበተው ኤዜ በቀጣይ ሁለት ቀናት ውስጥ ዝውውሩን ያጠናቅቃል ተብሏል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review