የመደመር መንግስት በሆደ ሰፊነት ለፖለቲካ ስክነትና መረጋጋት ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ

You are currently viewing የመደመር መንግስት በሆደ ሰፊነት ለፖለቲካ ስክነትና መረጋጋት ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ

‎AMN ነሐሴ 14/2017 ዓ.ም

‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመደመር መንግስት አስቻይ ሁኔታዎችን ዘርዝረዋል።

‎ከዚህም ውሥጥ አንዱ የሰከነ የፖለቲካ ስርዓት መሆኑን ጠቅሰዋል።

‎የመደመር መንግስት በሆደ ሰፊነት ለሰከነ ፖለቲካ ስርዓት መገንባት መሰረት የሚጥሉ በርካታ ስራዎችን ማከናወኑን አብራርተዋል።

‎ከመደመር መንግስት ተቃርነው በጥፋት መንገድ የቆሙ ሃይሎችን ጥፋታቸውን አምነው ከተመለሱ የመደመር መንግስት በይቅርታ ይቀበላቸዋል ብለዋል።

‎ሆደ ሰፊነት ለምናስበው የወል ግብ መሳካት ፋይዳው የጎላ ነው ሲሉም ነው የተናገሩት።

‎የመደመር መንግስት ከሰከነ ፖለቲካ ባሻገር ርዕይ መጋራትና እምነትን ማጽናት በትብብር ለሚደረግ ጥረት የልብ ምት መሆኑን እንደሚገነዘብም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርተዋል።

‎ሃሳብ አልባ ፖለቲካ፣ የተበላሸ የፖለቲካ ባህል፣ስሁት መረጃዎች፣ አፍቀሮተ ንዋይ፣ ጽንፈኝነት ከመደመር መንግስት ፈተናዎች መካካል መሆናቸውንም ዘርዝረዋል።

‎እነዚህን ፈተናዎች ለመሻገርም እውነትና እውቀት መሰረት ያደረገ የሃሳብ ገበያ፣ መርህን የሚከተል የተቋማት ግንባታ እንዲሁም አማራጭ እይታ እንዲጎለብት መስራት ይገባል ብለዋል።

‎በሔለን ተስፋዬ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review