ጉባኤው በወንጀል ድርጊት የተገኘ ሃብትን ህጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀሎችን ለመከላከል አቅም የሚፈጠርበት መሆኑን የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት አስታወቀ

You are currently viewing ጉባኤው በወንጀል ድርጊት የተገኘ ሃብትን ህጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀሎችን ለመከላከል አቅም የሚፈጠርበት መሆኑን የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት አስታወቀ

AMN ነሐሴ 15/2017

ጉባኤው በወንጀል ድርጊት የተገኘ ሃብትን ህጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀሎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ለሚደረገው ጥረት ተጨማሪ አቅም የሚፈጠርበት መሆኑን የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት አስታወቀ፡፡

ኢትዮጵያ ከነሐሴ 16 እስከ ነሐሴ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ የህገ ወጥ ገንዘብ ዝውውር ወንጀልን መከላከል ቡድን ዓመታዊ ጉባዔን ታስተናግዳለች።

የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ጉባዔውን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሀን መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በዚሁ ወቅት የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሙሉቀን አማረ እንደገለጹት፤ ጉባዔውን ማስተናገድ የሚያስቸል በቂ ዝግጅት ተደርጓል።

በጉባኤው ከ21 አባል ሀገራት የተውጣጡ የፋይናንስ ደህንነት ተቋማት እና አንድ ታዛቢ ሀገር እንዲሁም የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት እንደሚሳተፉ ጠቁመዋል።

በወንጀል ድርጊት የተገኘ ሃብትን ህጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀሎች ድንበር ተሻጋሪ እና የሚያስከትሉት ተጽዕኖ ዓለም አቀፍ መሆኑን ተናግረዋል።

ጉባዔው ቀጣናዊ ትብብርን ለማጠናከርና የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ከማገዙ ባሻገር ምክረ ሀሳቦች የሚቀርቡበት መሆኑንም አመላክተዋል።

ጉባዔው አለም አቀፋዊ ትብብር እና ቅንጅትን ለማጠናከር ጉልህ ሚና እንዳለውም ጠቁመዋል።

ጉባዔው በወንጀል ድርጊት የተገኘ ሃብትን ህጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀሎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ለሚደረገው ጥረት ተጨማሪ አቅም የሚፈጠርበት መሆኑን አንስተዋል።

ኢትዮጵያ ወንጀሉን ለመከላከል የፖለቲካ ቁርጠኝነት በመውሰድ እየሰራች መሆኑን ጠቁመው፤ ለዚህም ብሔራዊ ኮሚቴ አቋቁማ እንቅስቃሴ እያደረገች እንደምትገኝ አመልክተዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review