የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን እና አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

You are currently viewing የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን እና አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

AMN- ነሀሴ 15/2017

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን እና አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ስምምነቱን የተፈራረሙት የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ምክትል ስራ አስፈጻሚና የቴሌቪዥን ዘርፍ ሀላፊ አቶ ጥላሁን ካሳ እና የአዲስ አበባ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዲዳ ድሪባ ናቸው፡፡

የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ምክትል ስራ አስፈጻሚና የቴሌቪዥን ዘርፍ ሀላፊ አቶ ጥላሁን ካሣ፣ የትውልድ ድምፅ በመሆን በርካታ ጉዳዮችን ወደ ህዝብ እያደረሠ ያለው ተቋሙ፣ ከባልሥልጣኑ ጋር ያደረገው ስምምነት አዲስ አበባ ትኩረት ሠጥታ እያከናወነች ያለውን የአካባቢ ጥበቃ ስራ ተደራሽነትን ለማሰፋት ወሣኝ መሆኑን ጠቁመዋል።

የአዲስ አበባ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዲዳ ድሪባ፣ ኤ ኤም ኤን በሁሉም የስራ እንቅስቃሴያችን ሁሌም አብሮን ነው ያሉ ሢሆን፣ በአካባቢ ጥበቃ ስራ ላይ ለምንሰራቸው ማህበረሰቡን ያሣተፉ ስራዎች ከፍተኛ አስተዋጾ ያበረክታል ብለዋል።

በሥምምነቱ መሠረት አካባቢ ጥበቃ ላይ ትኩረት ያደረጉ ፕሮግራሞች በቴሌቪዥን፣ በሬድዮ እንዲሁም በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ወደ አድማጭ ተመልካች ይደርሳሉ።

በፀጋ ታደለ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review