የአሸንዳ በዓል በመቀሌ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው

You are currently viewing የአሸንዳ በዓል በመቀሌ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው
  • Post category:ባህል

AMN ነሐሴ 16/2017

የአሸንዳ በዓል በመቀሌ ከተማ የተለያዩ እንግዶች በተገኙበት በድምቀት እየተከበረ ነው።

የአሸንዳ በዓል በየዓመቱ በነሐሴ ወር አጋማሽ በወጣት ሴቶችና ልጃገረዶች በደመቀ ሁኔታ የሚከበር በዓል መሆኑ ይታወቃል።

በመቀሌ ከተማ እየተካሄደ ባለው የአሸንዳ በዓል አከባበር ስነ-ስርዓት ላይም የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)፣ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ እና ሌሎች እንግዶች መገኘታቸዉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በአሸንዳ በዓል ወጣት ሴቶችና ልጃገረዶች በተለያዩ ባህላዊ አልባሳት ደምቀው ልዩ ልዩ ጭፈራዎችን በማሳየት የሚያከብሩት በዓል ነው።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review