የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 5ኛ ዓመት 2ኛ መደበኛ ስብሰባ በዛሬው እለት አካሂዷል::

You are currently viewing የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 5ኛ ዓመት 2ኛ መደበኛ ስብሰባ በዛሬው እለት አካሂዷል::

ካቢኔው በዛሬው ውሎው በቀረቡ ሁለት ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ ውይይት በማድረግ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

በዚህ መሰረት፡-

1ኛ :-በኮሪደር እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ውስጥ የመንግስትና የግል አጋርነት ጽ /ቤት የተፈረመውን ስምምነት ለሚለሙ 30 ፕሮጀክቶች ከ733 ቢሊዬን ብር በላይ ወጪ ፣ 27 አልሚዎችን ፤ ዉጤታማ ለማድረግ ካቢኔዉ መርምሮ እንዲያፀድቅ የቀረበለት አጀንዳ በመወያየት ፣ካላቸው ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ፣ የሚፈጥሩት ሰፊ የስራ እድል እና ከተማን ትብብር የማልማት ትልቅ ፋይዳ እና አዲስ አሰራር በመሆኑ ከቢኔው በቀረበ የዉሳኔ ሀሳብ ላይ ውይይት በማድረግ ውሳኔ አፅድቋል፡፡

2ኛ :-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የአሰልጣኞች የዝውውርና የምደባ አፈፃፀም ደንብ በተመለከተ በቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት ጥራት ያለው ሥልጠና ለመስጠት፣ ኮሌጆቿን ውጤታማ ከማድረግ እና በተደራጀ አግባብ ለመምራት በሚያስችል መልኩ የደንቡ መውጣት እገዛው የጎላ በመሆኑ ውይይት በማድረግ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review