ባለፋት ሁለት ወራት በመዲናዋ በምርት አቅርቦት እና በህገ ወጥ ንግድ ቁጥጥር ላይ ውጤታማ ስራ መሰራቱ ተገለጸ

You are currently viewing ባለፋት ሁለት ወራት በመዲናዋ በምርት አቅርቦት እና በህገ ወጥ ንግድ ቁጥጥር ላይ ውጤታማ ስራ መሰራቱ ተገለጸ

AMN – ነሐሴ 17/2017 ዓ.ም

ባለፋት ሁለት ወራት በአዲስ አበባ ከተማ በምርት አቅርቦት፣ በፍጆታ አቃዎች ስርጭት፣ በኮንትሮባንድ ቁጥጥር፣ በህገ ወጥ ንግድ ቁጥጥርና ሌሎች ዘርፎች አበረታች ውጤት መገኘቱን የአዲስ አበባ ከተማ የህግ ማስከበርና ቁጥጥር ንኡስ ኮሚቴ አስታውቋል::

ኮሚቴው፣ የሁለት ወራት ተግባራትን ሪፖርትና የቀጣይ የትኩረት አቅጣናችን በተመለከተ ምክክር አድርጓል።

በሂደቱም ያለንግድ ፈቃድ መነገድ፣ የቅዳሜና እሁድ ገበያ ቁጥጥር፣ ያለደረሰኝ መነገድን፣ የምሽት የንግድ እንቅስቃሴ እና ሌሎች የኮንትሮባንድ ንግድ እንቅስቃሴዎች የቁጥጥር ስራዎች ዋና ዋና የትኩርት አቅጣጫዎች እንደነበሩ ተገልጿል::

በዚህም ባለፋት ሁለት ወራት በምርት አቅርቦት፣ በኮንትሮባንድ ንግድ ቁጥጥር ፣ በህገ ወጥ ንግድ ቁጥጥር፣ በቅዳሜና እሁድ ገበያዎች እንዲሁም ሌሎች ዘርፎች አበረታች ውጤት መገኘቱም ተመላክቷል።

በቀጣይም የምርት ተደራሽነት ማሻሻልና የፍጆታ እቃዎች ስርጭት በተገቢው ሁኔታ ተደራሽ ማድረግ፣ ከደመወዝ ማሻሻያው ጋር ተያይዞ ያለ አግባብ ጭማሪ የሚያደርጉ የንግድ ተቋማትና ግለሠቦች ላይ አስተማሪና የማያዳግም እርምጃ መወሰድ እንዳለበት አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

ኮሚቴው፣ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ፣ የንግድ ቢሮ፣ የገቢዎች ቢሮ እንዲሁም የደንብ ማስከበር ባለስልጣንን ያካተተ መሆኑም ተገልጿል፡፡

በአንዋር አህመድ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review