ብሔራዊ ጥቅማችንን ለማስጠበቅ የተቋማት ግንባታን ማጠናከር ይገባል ሲል ብልጽግና ፓርቲ ገለጸ

You are currently viewing ብሔራዊ ጥቅማችንን ለማስጠበቅ የተቋማት ግንባታን ማጠናከር ይገባል ሲል ብልጽግና ፓርቲ ገለጸ

AMN ነሐሴ 17/2017

“ወደ ተምሳሌት አገር በተሻገር ሕልም፤ በላቀ ትጋት አስተማማኝ ስራ መስራት” በሚል መሪ ቃል ለአራት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የነበረው የፌዴራል ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች ስልጠና መድረክ ተጠናቋል፡፡

ፓርቲው የስልጠና ማጠቃለያውን በተመለከተ ለኢዜአ በላከው መልዕክት ብሔራዊ ጥቅማችንን ለማስጠበቅ የተቋማት ግንባታን ማጠናከር ይገባል ብሏል።

የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አደም ፋራህ እንደገለጹት ብሔራዊ ጥቅምን ለማስጠበቅ የተቋማት ግንባታ ማጠናከር ይገባል ነው ያሉት፡፡

በሁሉም ተቋማት የአገልግሎት ልህቀት ማረጋገጥ የሚያስችል ስራ መስራት እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡

ብሔራዊ ጥቅምን ለማሳካት ከሌሎች አካላት ጋር የሚኖረውን ግንኙነት ሚዛናዊ እይታና ተራማጅ መሆን እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

አካታች ተቋማትን በመገንባትና ሲቪል የሪፎርም ስራዎችን በማጠናከር የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ በባለቤትነት መንፈስ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የውስጠ ፓርቲ አንድነት፣ ጥንካሬና ጥራት ማረጋገጥ ከፋፋይና ሰርጎገብ አጀንዳዎችን መታገል እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡

አመራሩ የብልጽግና እሴቶችን በመላበስ ለሕዝብ የገባናቸው ቃሎች በተግባር በመፈጸም ውጤታማነትን ማረጋገጥ ይገባል ሲሉ መናገራቸዉን ኢዜአ ዘግቧል።

አስተሳሳሪና ገዥ ትርክትን በመጠቀም በየተቋሙ ያሉ ውስጣዊ ችግሮችን በመፈተሽና በእቅድ በመምራት ሃላፊነትን በአርአያነት መወጣት እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review