የአሸንዳ በዓልን በነፃነትና በልዩ ደስታ እንደሚያከብሩት የበዓሉ ተሳታፊዎች ገለፁ

You are currently viewing የአሸንዳ በዓልን በነፃነትና በልዩ ደስታ እንደሚያከብሩት የበዓሉ ተሳታፊዎች ገለፁ

AMN- ነሀሴ 17/2017

የአሸንዳ በዓልን በልዩ ናፍቆትና ደስታ በነፃነት እንደሚያከብሩት በመቀሌ እየተከበረ ባለው በዓል ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ ወጣት ሴቶች ገለፁ።

የአሸንዳ በዓል በየዓመቱ በነሐሴ ወር አጋማሽ ላይ በወጣት ሴቶችና ልጃገረዶች በደመቀ ሁኔታ የሚከበር በዓል ነው።

ልጃገረዶቹ የአሸንዳ በዓልን ባህላዊ እሴቱን በጠበቀና ነባር ትውፊቶቹን በሚያንፀባርቅ መልኩ በደመቀ ሁኔታ በማክበር ላይ ናቸው።

ከበዓሉ ተሳታፊዎች መካከል ወጣት ፊዮሪ ገብረስላሴ፤ የአሸንዳ በዓል እሴቶች ተጠብቀው እንዲቆዩ ሴቶች ጠንክረን በባህላችን ላይ ልንሰራ ይገባል ብላለች።

የአሸንዳ በዓል ይዘቱን እንደጠበቀ ለቀጣይ ትውልድ እንዲተላለፍ እኛም ሚና አለን ያለችው ደግሞ ሌለኛዋ ተሳታፊ ወጣት ሸገ አሸናፊ ናት።

የበዓሉ መገለጫ የሆኑ ባህላዊ እሴቶች እንዳይበረዙ ጠንክረን ልንንቀሳቀስ ይገባልም ብላለች።

ወጣት ህይወት በርሄ በበኩሏ የአሸንዳ በዓል ከአለባበስ ጀምሮ የፀጉር አሰራርና ባህላዊ ጌጣጌጥ ተውበው በማክበር ላይ መሆናቸውን መናገሯን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡

የአሸንዳ በዓል በክልል ደረጃ የክልሉን ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጨምሮ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ(ዶ/ር)፣የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ እና ሌሎች እንግዶች በተገኙበት ትናንት በመቀሌ ከተማ በደማቅ ሁኔታ መከበሩ ይታወሳል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review