ሰሜን ኮሪያ አዲስ የሚሳኤል ሙከራ ማድረጓን አስታወቀች

You are currently viewing ሰሜን ኮሪያ አዲስ የሚሳኤል ሙከራ ማድረጓን አስታወቀች

AMN – ነሐሴ 18/2017 ዓ.ም

ሰሜን ኮሪያ የሃገሪቱ መሪ ኪም ጆንግ ኡን በተገኙበት ሁለት አዲስ የአየር መከላከያ ሚሳኤሎች ሙከራ ማድረጓን የኮሪያ መንግስት ሚዲያ አስታውቋል፡፡

የአየር መከላከያዎቹ ለየት ያለ ቴክኖሎጂ የተገጠመላቸው እና ከፍተኛ አቅም ያላቸው እንደሆኑ እና ሰው አልባ ድሮኖችን እና ክሩዝ ሚሳኤሎችን ጨምሮ የተለያዩ የአየር ላይ ጥቃቶች መከላከል እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡

ሙከራው የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ከደቡብ ኮሪያ ጋር ወደሚያዋስናቸው ከወታደራዊ ሃይል ነፃ የሆነ ክልል መሻገራቸውን ተከትሎ ደቡብ ኮሪያ የማስጠንቀቂያ ተኩሶችን ከሰነዘረች ከቆይታዎች በኋላ ነው፡፡

ሰሜን ኮሪያም የደቡብ ኮሪያን ተኩስ ሆን ተብሎ የተደረገ ቅስቀሳ ስትል ገልፃዋለች፡፡

ደቡብ ኮሪያ እና አሜሪካ በክልሉ መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ልምምዶች እያደረጉ መሆናቸውን ኪም ጆንግ ኡን በጥሩ እይታ አለማየታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ይህንን ተከትሎም የሃገሪቱ የኒውክሌር መሳሪያ እድገትን እንደሚያጠናክሩ ኪም ገልፀዋል፡፡

የደቡብ ኮሪያ ከፍተኛ ባለስልጣናት፤ ሰሜን ኮሪያ ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምትሰነዝረውን ጥቃት ለመደገፍ ወታደሮቿን ወደ ሩሲያ መላኳን ተከትሎ የሩሲያ ሚሳኤል ቴክኖሎጂን ስለማግኘቷ ያላቸውን ስጋት ገልፀዋል፡፡

ሆኖም የሚሳኤል ሙከራው እነዚህን ከሩሲያ ተገኙ የተባሉትን ሚሳኤሎች ያካተተ ስለመሆኑ አልተረጋገጠም፡፡

በሊያት ካሳሁን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review