በአማራ ክልል የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እና ብልፅግናን እውን ለማድረግ በየደረጃው ያለው አመራር በቁጭት መስራት እንዳለበት ተገለጸ

You are currently viewing በአማራ ክልል የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እና ብልፅግናን እውን ለማድረግ በየደረጃው ያለው አመራር በቁጭት መስራት እንዳለበት ተገለጸ

AMN ነሐሴ 18/2017

በአማራ ክልል የህዝብን የላቀ የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና ብልፅግናን እውን ለማድረግ በየደረጃው ያለው አመራር በቁጭት መስራት እንዳለበት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ገለጹ።

”አርቆ ማየት፤አልቆ መስራት ለህዝባችን ከፍታ” በሚል መሪ ሀሳብ የአመራር ውይይት በባህር ዳር ከተማ ዛሬ መካሄድ ጀምሯል።

መድረኩ የክልሉን የ25 ዓመት አሻጋሪ የልማት ፍኖተ ካርታ እና የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ ያተኮረ መሆኑም ተመላክቷል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ እንደገለጹት፥ ክልሉን አሁን ካለበት ተግዳሮት በማላቀቅ ህዝቡን በየደረጃው ተጠቃሚ የሚያደርግ እድገት ማስመዝገብ ይገባል።

ለዚህም የሚገጥሙ ወቅታዊ ችግሮችን በላቀ አመራር ሰጭነትና ጥበብ በመሻገር የክልሉን ህዝብ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ተጠቃሚነቱን ለማላቅ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ለእዚህም የአጭርና የረጅም ጊዜ ዕቅድ ተይዞ ወደ ተግባር መገባቱን ጠቁመው፥ ለስኬታማነቱም በየደረጃው ያለው አመራር በቁጭት ተግቶ ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ሀላፊ ደመቀ ቦሩ (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ የበለፀገ ህዝብና ክልል ለመገንባት የሚከናወኑ የልማት ሥራዎች ስኬታማ እንዲሆን የልማት ዕቅዶችን በተባበረ ክንድ ማከናወን ይገባል ብለዋል።

ለዚህም አሻጋሪ የሆነ የረጅም ጊዜ ዕቅድ ተነድፎ ወደ ትግበራ መገባቱን የገለጹት ሃላፊው፣ ለስኬታማነቱ ህዝቡን በነቂስ በማሳተፍ መስራት እንደሚገባ መናገራቸዉን ኢዜአ ዘግቧል።

ከዛሬ ጀምሮ እስከ ነሐሴ 26 ቀን 2017 በሚቆየው በዚህ መድረክ ላይ የክልሉ አመራሮችን ጨምሮ በየደረጃው ያሉ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች እየተሳተፉ መሆናቸው ታውቋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review