ወጣቶች በተደመረ አቅም ለኢትዮጵያ ብልጽግና የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ ሊያጠናክሩ እንደሚገባ ተገለፀ

You are currently viewing ወጣቶች በተደመረ አቅም ለኢትዮጵያ ብልጽግና የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ ሊያጠናክሩ እንደሚገባ ተገለፀ

AMN – ነሐሴ 18/2017 ዓ.ም

ወጣቶች በተደመረ አቅም በመንቀሳቀሰ ለኢትዮጵያ ብልጽግና የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ ሊያጠናክሩ እንደሚገባ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ገለጹ።

የዓለም ዓቀፍ የወጣቶች ቀን “የተደመረ የወጣቶች አቅም ለዘላቂ ልማት ግቦች ስኬት” በሚል መሪ ሀሳብ የፌደራልና የክልል የስራ ኃላፊዎች፣ ወጣቶች የወጣት አደረጃጀቶች መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት በተገኙበት እየተከበረ ይገኛል።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፤ የወጣቶችን ተጠቃሚነትና ተሳትፎ የሚያረጋግጡ በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ ነው።

የወጣቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ የፖሊሲ ዝግጅቶች፣ የአደረጃጀት ምቹ ሁኔታ መፍጠር፣ የስራ ፈጠራ ስራዎች፣ የትምህርት ጥራትና ተደራሸነት፣ ወጣት ተኮር የጤና አገልግሎቶችና ሌሎች በርካታ ስራዎችን ጠቅሰዋል።

ወጣቶች በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፖለቲካ ዘርፎችም ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ እንደሚገኙ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወጣቶች በተደመረ አቅም በመንቀሳቀስ ለኢትዮጵያ ብልጽግና የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ ሊያጠናክሩ እንደሚገባ ጠቁመው፤ የአጋር አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ማደግ እንዳለበት ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ፉአድ ገና በበኩሉ፤ የወጣቶችን ቀን የምናከብረው ለመገንባት የምንመኛትን ኢትዮጵያ በተደመረ የወጣቶች አቅም እውን ለማድረግ በማለም ጭምር ነው ብሏል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review