የኩሙሩክ የወርቅ ፋብሪካ በምስራቅ አፍሪካ ትልቁ ሊሆን እንደሚችል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡
የኩሙርክ ወርቅ ፋብሪካ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኝ ሲሆን 20ኪሎ ሜትር የመሬት ስፋት የያዘ ነዉ።
በምስራቅ አፍሪካ ትልቁ እንደሆነ የተነገረለት ይህ የወርቅ ፋብሪካ በሚቀጥለው አመት ስራ እንደሚጀምር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልፀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኩሙሩክ የወርቅ ፋብሪካ እና የአሶሳ ከተማ የኮሪደር ልማት የደረሰበትን ደረጃ የተመለከቱ ሲሆን፣ የወርቅ ፋብሪካዉ በምስራቅ አፍሪካ ትልቁ ፋብሪካ ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል።
ክልሉ ሰፊ የወርቅ አቅም እንዳለው የሚያሳይ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከባለፈው አመት ጉብኝታችን በኋላ ያየነው እድገት የሚበረታታ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል።

ፕሮጀክቱ ሙሉ በሙሉ በሚጠናቀቅበት ጊዜ በጎ ተጽዕኖው በመላው ክልሉ እንደሚታይ ገልፀዋል፡፡
መሰል ስራዎች ከሌሎች ፕሮጀክቶች ጋር ተደምረው የሀገራዊ ብልጽግናችን መገንቢያ ጡቦች ናቸው ብለዋል።
ማዕድን በብዝኃ ዘርፍ የልማት ምልከታችን አንዱ ቁልፍ ዘርፍ ሆኖ ይቀጥላል ሲሉም ተናግረዋል።
በፋብሪካው በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን የያዙ መጠለያዎች መኖራቸውን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ እጅግ ዘመናዊ ፋብሪካ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የኩሙሩክ ወርቅ ፋብሪካ በሚቀጥለው አመት አጋማሽ በኋላ ወደ ምርት እንደሚገባ ጠቁመው፤ ከዚያኛው አመት በኋላ የሚመረተው ወርቅ በአመት እስከ አንድ ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚያስገኝ ግዙፍ ፕሮጀክት ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስረድተዋል።
የኮሪደር ልማቱንም አስመልክተዉ፤ ዛሬ በከተማዋ ያየነው ባለፈው አመት ካየነው በፍፁም ተቃራኒ ነው ሲሉ ገልፀዋል።
የተለወጠበት መንገድ ጥሩ ጅማሮ እንደሆነ የኮሪደር ሥራ ውጤቱ የሚታይ ነው ብለዋል።
በሔለን ተስፋዬ