ትምህርት የአፍሪካን የለውጥና የመነሳት ጉዞ እንዲመራ ለአንድ ዓላማ በጋራ መስራት እንደሚገባ ተመስገን ጥሩነህ አስገነዘቡ

You are currently viewing ትምህርት የአፍሪካን የለውጥና የመነሳት ጉዞ እንዲመራ ለአንድ ዓላማ በጋራ መስራት እንደሚገባ ተመስገን ጥሩነህ አስገነዘቡ

AMN- ነሐሴ 19/2017 ዓ.ም

ትምህርት የአፍሪካን የለውጥና የመነሳት ጉዞ እንዲመራ ለአንድ ዓላማ በጋራ መስራት አለብን ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አስገንዝበዋ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ዛሬ ኢትዮጵያ እያስተናገደች ያለውን 41ኛውን የአፍሪካ የትምህርት ምዘና ዓመታዊ ጉባኤን በይፋ መክፈታቸውን ገልጸዋል።

አፍሪካ እያደገች ነው፤ ነገር ግን ይህ በቂ አይደለም የመጪው ዘመን መሪ ልትሆን ይገባል በማለትም አክለዋል።

ለዚህ ደግሞ የአፍሪካ ልጆች የመማር እድልን ብቻ ሳይሆን ፍትሐዊ፣ ተገቢ እና ጥራት ያለው ትምህርት ማግኘታቸውን ማረጋገጥ አለብን ብለዋል።

የትምህርት ምዘና መማርን የምንለካበት ብቻ ሳይሆን፣ ያለንበትን የሚነግረንና ወደየት መሄድ እንዳለብን የሚመራን ቁልፍ መሳሪያ መሆኑንም ነው ያነሱት።

ኢትዮጵያ የትምህርትና የምዘና ስርዓቷ ፍትሐዊ፣ ትርጉም ያለው እና በንድፈ ሀሳብ እውቀት ብቻ ሳይሆን በተግባራዊ ክህሎቶች ላይ ያተኮረ እንዲሆን ልዩ ትኩረት ሰጥታ እየሠራች መሆኑንም አመላክተዋል።

በሁሉም መስክ የተሻለች አፍሪካን ለመገንባት ለትምህርት ጥራት ቅድሚያ ልንሰጥ ይገባል ሲሉም አፅንዖት ሰጥተዋል።

ለዚህም አህጉራዊ አንድነትን የሚያጠናክር፣ ባህላዊ ዕውቀትን የሚያከብር፣ አፍሪካዊ እውቀትን መቅሰም የሚያስችል የጋራ አህጉራዊ የትምህርትና የምዘና ስርዓት መፍጠር እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review