ትምህርትን ከገንዘብ ጋር ማያያዝ ትውልድ እና ሀገርን ይጎዳል ሲሉ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገለጹ

You are currently viewing ትምህርትን ከገንዘብ ጋር ማያያዝ ትውልድ እና ሀገርን ይጎዳል ሲሉ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገለጹ

AMN- ነሀሴ 19/2017 ዓ.ም

የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ትምህርትን ከገንዘብ ጋር ማያያዝ ትውልድ እና ሀገርን እንደሚጎዳ ገልፀዋል።

በዳግም ምዝገባ አፈፃፀም ዙሪያ ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር የውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ የተገኙት የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ(ፕ/ር)፤ ትምህርት በሀገር ዕድገት ላይ ቁልፍ ሚና ያለው በመሆኑ ዘርፉን በጥራት እና በልዩ ትኩረት መምራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

ትምህርትን ከገንዘብ ጋር ማያያዝ ሀገርንና ትውልድን ይጎዳል ያሉ ሲሆን በአዲሱ የ2018 ትምህርት ዘመን በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ወሳኝ እርምጃዎች ይወሰዳሉ ብለዋል።

የዳግም ምዝገባ ዓላማው በአዲሱ የፈቃድ አሰጣጥ ስታንዳርድ መሰረት ለመገምገም፣ ለመመዝገብ፣ ተዛማጅ ካልሆነ የንግድ ተቋማት ጋር ተቀላቅለው እንዳይሰሩ፣ ሰነዶቻቸውን በአዲሱ የጥራት መስፈርት መሰረት እንዲከልሱ፣ የመምህራኖቻቸውን የትምህርት ዝግጅትና የቅጥር ሁኔታ በሚፈለገው ደረጃ እንዲያስተካክሉ፣ ማህበረሰቡ ጥራት ያለው ትምህርት እንዲያገኝና ችግር ፈቺ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን ለማድረግ አስቻይ መሆኑን በመድረኩ በቀረበ ሰነድ ተገልጿል።

በማሬ ቃጦ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review