የኮሎምቢያ ምክትል ፕሬዚዳንት ፍራንሲያ ማርኬዝ አዲስ አበባ ገቡ

You are currently viewing የኮሎምቢያ ምክትል ፕሬዚዳንት ፍራንሲያ ማርኬዝ አዲስ አበባ ገቡ

AMN ነሐሴ 19/2017

የኮሎምቢያ ምክትል ፕሬዚዳንት ፍራንሲያ ማርኬዝ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ።

ምክትል ፕሬዚዳንቷ ቦሌ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ምክትል ፕሬዚዳንቷ በቆይታቸው ከኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር የሁለቱ አገራት ግንኙነት ይበልጥ በሚጠናከርባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።

ኢትዮጵያና ኮሎምቢያ በ2015 ዓ.ም በፖለቲካ ምክክርና በሌሎች የትብብር መስኮች በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወቃል።

ሁለቱ ሀገራት ይፋዊ የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩት እ.አ.አ በ1947 መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review