በቻይና የተካሄደው የክህሎት ውድድር ኢትዮጵያ በዘርፉ ያላትን እምቅ አቅም ያሳየችበት መሆኑ ተገለፀ

You are currently viewing በቻይና የተካሄደው የክህሎት ውድድር ኢትዮጵያ በዘርፉ ያላትን እምቅ አቅም ያሳየችበት መሆኑ ተገለፀ

AMN – ነሐሴ 19/2017 ዓ.ም

በቻይና የተካሄደው የክህሎት ውድድር ኢትዮጵያ በዘርፉ ያላትን እምቅ አቅም ያሳየችበት መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ። በቻይና ጎዋንዡ ከብሪክስ አባል ሀገራት ከተውጣጡ ከ300 በላይ ተሳታፊዎች የተሳተፉበት የክህሎት ውድድር ተካሂዷል፡፡

ኢትዮጵያን በመወከል በውድድሩ ያሸነፉት ተወዳዳሪዎች ሀገራችን በክህሎት ልማት ላይ እየሰራች እንዳለ በዓለም የክህሎት አደባባይ ያረጋገጡበት እንደሆነ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገልጸዋል። ሚኒስትሯ በቻይና በተካሄደ የክህሎት ውድድር አሸናፊ የሆኑትን ወጣቶች በቢሯቸው አቀባበል አድርገውላቸዋል። በውድድሩ የተሳተፉት ኢትዮጵያዊያን የወርቅ፣ የብርና የነሐስ ሜዳሊያ አሸናፊ መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ለ11ኛ ዙር በቻይና ጎዋንዡ በተካሄደው ውድድር ላይ ኢትዮጵያን ወክለው ከተወዳደሩት ወጣቶች መካከል ዘላለም እንዳለው 1ኛ በመውጣት የወርቅ ሜዳሊያ፣ አቤኔዘር ተከስተ 2ኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ አሸናፊ ሲሆን፤ ነቢሀ ነስሩ 3ኛ በመውጣት የነሐስ ሜዳሊያ አግኝተዋል። የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ከለውጡ ወዲህ መንግስት በክህሎት ልማት ላይ በትኩረት እየሰራ ነው።

በዚህ አበረታች ውጤት እየተመዘገበ እንዳለ አንስተው፤ በዓለም አደባባይ በመወዳደር ሀገርን ማስጠራት እየተቻለ ነው ብለዋል። በቻይና የተካሄደው የክህሎት ውድድር ኢትዮጵያ ያላትን እምቅ አቅም ያሳየችበት መሆኑን ተናግረዋል። ሌሎች ወጣቶች ክህሎታቸውን በማወጣት እና ተቋማት በጋራ መስራታ ከቻሉ የበለጠ ውጤት እንደሚያመጡ ገልጸዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review