ኢትዮ-ቴሌኮም አዳዲስ እይታዎችን እና ፈጠራዎችን ያካተተ የሶስት ዓመታት ስትራቴጂ ዕቅድ ይፋ አደረገ

You are currently viewing ኢትዮ-ቴሌኮም አዳዲስ እይታዎችን እና ፈጠራዎችን ያካተተ የሶስት ዓመታት ስትራቴጂ ዕቅድ ይፋ አደረገ

AMN – ነሐሴ 20/2017 ዓ.ም

ኢትዮ-ቴሌኮም አዳዲስ እይታዎችን እና ፈጠራዎችን ያካተተ የሶስት ዓመታት ስትራቴጂ እና አመታዊ ዕቅድ ይፋ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

“አድማስ” የሚል ስያሜ የተሰጠው ስትራቴጂው ከ2018 እስከ 2020 ዓ.ም ድረስ የሚተገበር መሆኑም ተገልጿል።

ስትራቴጂውን አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡት የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ፣ ተቋሙ ከቴሌኮም ያለፈ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ጠቁመው፣ አዲሱ ስትራቴጂ አገልግሎቱን በተሻለ ደረጃ ለማከናወን የሚረዳ ነው ብለዋል።

አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን የመታጠቁ ሁኔታ ቀጣይነት እንደሚኖረው ያመላከቱት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ፣ አዲሱ ስትራቴጂ ተወዳዳሪ ለመሆን ብቻ ሳይሆን በብቃት መስራት እንደሚገባ አመላካቶችን እንዳካተተ ተናግረዋል።

ስትራቴጂው በውስጥ አቅም የተቃኘ መሆኑን የጠቆሙት ዋና ስራ አስፈጻሚዋ፣ የመፈጸም እና የማስፈጸም አቅም እንዲሁም ሌሎች ግብዓቶች ታክለውበት ትርጉም ያለው እድገት እንደሚያረጋግጥ ገልጸዋል።

ስትራቴጂው ከኢትዮጵያ ገበያ ባሻገር ያለውንም የሚመለከት እና አዲስ የገቢ ምንጭ ብቻ ሳይሆን የእድገት ምንጮችን ያካተተ እና የተጠቃሚዎች እርካታ ከግምት ውስጥ ያስገባ መሆኑም ተመላክቷል።

ኢትዮ- ቴሌኮም በ2018 በበጀት አመት 235.8 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ማቀዱንም የተቋሙ ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል።

በሶስት አመታቱ የስትራቴጂክ እቅድ የደንበኞችን ቁጥር 100 ሚሊዮን እንዲሁም የቴሌብር ተጠቃሚዎችን ደግሞ 75 ሚሊዮን ለማድረስ መታቀዱንም አክለዋል።

በተጨማሪም በሶስት አመታቱ የአድማስ ስትራቴጂክ እቅድ 842.3 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱም ተመላክቷል።

በሀብታሙ ሙለታ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review