በአሜሪካ አሪዞና ግዛት የተከሰተው አውሎ ንፋስ በርካታ ጉዳቶችን ማስከተሉን ቢቢሲ በዘገባው አስነብቧል፡፡
“ሀቦብ” በመባል የሚታወቀውና በሰዓት 50 ማይል እንደሚጓዝ የተነገረለት ይህ አውሎንፋስ የአቧራ ደመና የፈጠረ ሲሆን፣ በአሪዞና እና በአካባቢው የኤሌክትሪክ መበራቶች እንዲቋረጡ አድርጓል፡፡
በዚህ ምከንያት አካባቢው በጨለማ እንዲዋጥ ከማድረጉም ባለፈ፣ የአውሮፕላን በረራዎችም እንዲስተጓጎሉ ሆነዋል፡፡
በአንዳንድ የአሪዞና እና ምስራቃዊ ካሊፎርኒያ አካባቢዎችም ድንገተኛ የጎርፍ አደጋ ሊከሰት ይችላል በማለት ማስጠንቀቂያዎች እንደተሰጡ መረጃው ያመላክታል፡፡
የአሪዞና የትራንስፖርት ዲፓርትመንትም፣ አሽከርካሪዎች የአቧራ ደመና ወደ ፈጠረው አውሎ ነፋስ እንዳያመሩ ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ዘገባው አስነብቧል፡፡
በአስማረ መኮንን