የኢትዮጵያን የቴምር ልማት ለተቀረው ዓለም የሚያስተዋውቀው ፌስቲቫል

You are currently viewing የኢትዮጵያን የቴምር ልማት ለተቀረው ዓለም የሚያስተዋውቀው ፌስቲቫል

AMN- ነሐሴ 20/2017 ዓ.ም

ኢትዮጵያ በቴምር ልማት እየሰራች ያለውን ሥራ የሚያስተዋውቅ የመጀመሪያው ዓለም ዓቀፍ የቴምር ፌስቲቫል በአፋር ክልል ሠመራ ከተማ በርካታ ተሳታፊዎች በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

ዛሬን ጨምሮ ለሶስት ቀናት በሚቆየው ዓለም አቀፍ ፌስቲቫል፣ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባን ጨምሮ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ መለሰ መኮንን (ዶ/ር)፣ በኢትዮጵያ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ አምባሳደር ተወካይ ራሽድ አብደላ ሻይ እና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው ታዳሚዎች ተገኝተዋል።

በተጨማሪም በቴምር ዘርፍ የተሰማሩ እና ከተባበሩት አረብ ኢምሬት የከሊፋ ኢንተርናሽናል አዋርድ ፎር ዴት ፓልም ኤንድ አግሪካልቸር ኢኖቬሽን፣ ከሳዑዲ እና ሌሎች አገራትም በርካቶች ተሳትፈዋል።

ቴምር፣ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በሞቃታማ አካባቢ የሚበቅል ፍሬ ነው።

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ቴምር ከምግብነት ባለፈ ዘርፈ ብዙ የጤና ጥቅሞች እንዳሉት በጥናት ተረጋግጧል።

በዚህም በብዙዎች ዘንድ በጣም ተወዳጅ እና ተመራጫ እየሆነ መጥቷል፡፡

ለምዕራብ ሀገራት ለገበያ የሚቀርበው የቴምር ዓይነት ሁሉም በሚባል ደረጃ ደረቅ ነው።

ቴምርን መድረቅና አለመድረቁን በመልኩ ማወቅም ይቻላል።

ቆዳው የተሸበሸበ ከሆነ መድረቁን የሚያመለክት ሲሆን፣ ለስላሳ ከሆነ ደግሞ ትኩስነቱን ያሳያል።

እንደየዝርያቸው ትኩስ ቴምሮች መጠናቸው አነስተኛ ሲሆኑ፤ ቀለማቸው ወቅቱን ጠብቆ ከደማቅ ቀይ እስከ ደማቅ ቢጫ ይደርሳል።

በብዛት ጥቅም ላይ የሚውሉት የቴምር ዝርያዎች ሜጁል (Medjool) እና ዴግሌት ኑር (Deglet Noor) የሚሰኙትን ያካትታሉ።

ቴምር ታኝኮ የሚበላ ጣፋጭ ጣዕም ያላው የፍሬ ዓይነት ሲሆን፤ በውስጡ የተለያዩ ጥቅሞችን የሚሰጡ በጠቃሚ ንጥረ ነገሮች የበለፀገ ነው።

ቴምር ለሰውነት በጣም ገንቢ ንጥረ ነገር የያዘ መሆኑን እና ዘርፈ ብዙ ጥቅም እንዳለው የሄልዝ ላየን ዘገባ ያመለክታል፡፡

ለሶሰት ቀናት በሚካሄደው ፌስቲቫል የተሻሻሉ የቴምር ዝርያዎች በተሞክሮነት ቀርበው የሚታዩ ሲሆን፣ በዘርፉ ልማት የተሞክሮ ልውውጥም ይደረጋል፡፡

በታምራት ቢሻው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review