የወተት አከፋፋዩ ወጣት ህይወት ቀያሪ ትጋት

You are currently viewing የወተት አከፋፋዩ ወጣት ህይወት ቀያሪ ትጋት

AMN-ነሀሴ 21/2017 ዓ/ም

የላፍቶዋ ሠገነት ተራራ ለአካባቢው አርሶ አደሮች እንደ ቤት ለነዋሪዎች እንደ ወተት ምንጭነት ስትታይ ቆይታለች። ሰገነት ተብላ በምትጠራው አካባቢ ከጥንት ጀምሮ አርሶ አደሮች ከትመው ወተት እንደ ውሃ ይጠጡባት ነበር። ልጆቻቸውም የአባቶቻቸውን ፈለግ በመከተል የከተማ ግብርናውን ለፍሬ እያበቁ ይዘውት ቆይተዋል። ወጣት አርሶ አደር መከታ ፍቅሬና ቤተሰቦቹም ታዲያ ተስፋ ሳይቆርጡ እና ለድህነትም እጅ ሳይሰጡ ሲታገሉ የለውጡ ብርሃን ፈነጠቀላቸው።

የሰገነት የእንስሳትና የወተት እርባታ ድርጅት ባለቤት ወጣት አርሶ አደር መከታ ፍቅሬ የከተማ ግብርና ስራ ለዘመና ተዳክሞ እንደነበር ያስታውሳል። ለውጡን ተከትሎ ግን ተስፋው መለምለሙን ለአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ዲጂታል ሚዲያ ተናግሯል። ምክንቱም ለውጡ ለከተማ ግብርና እና ለሌማት ትሩፋት ትኩረት መስጠት በመቻሉ ነው፡፡ በዚህም የተሻለ ዕድል በመፈጠሩ እና ሙያዊና አስተዳደራዊ ድጋፎች በመደረጋቸው የከተማ ግብርና ሥራ ሕይወት መዝራት መቻሉን ይገልጻል።

ወተት በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ የገቢ ምንጭ የፈጠረው ወጣቱ አርሶ አደር መከታ ራሱንና ቤተሰቡን በሚገባ ከማስተዳደር አልፎ በአከካቢው ላሉ ወተት ፈላጊ ነዋሪዎች እፎይታን ሰጥቷል። በቀን 480 ሊትር ወተት የሚያመርት ሲሆን ለ42 ዜጎችም የስራ እድል ፈጥሯል። የወጣቱ አርሶ አደር ቤተሰብ የገቢ አቅምም የተሻለ ደረጃ ላይ ደርሷል። የህይወቱን መነሻ ጠንቅቆ የሚያውቀው ወጣቱ አርሶ አደር ገበያውን በማረጋጋት ሂደትም ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ ነው የተናገረው። በቀጣይም የከተማዋን ህዝብ የወተት ፍላጎት የመሸፈን ውጥን እንዳላቸውም ወጣት መከታ ያስረዳል።

የስራ እድል በመፍጠር ተጓደኝ የከተማ ግብርናን በማስፋፋት የእንቁላል ምርትና የእንስሳት መኖ በፋብሪካ የማቀነባበር እቅዱን ለማሳካት እየተጋሁ ነኝ ብሏል። ወተት እና የወተት ተዋፅዖዎችን በመግዛት ደንበኛ የሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች ያለስጋት ንፁህ ወተትና አይብ እያገኙ መሆኑን ገልፀው ለህጻናትና ለአዋቂዎች ጤና ተስማሚ ነው ብለዋል። ይህ መንግስት ለከተማ ግብርና የሰጠውን ትኩረት ያመለክታል ያሉት ነዋሪዎች ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ተናግረዋል።። በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰለሞን ፈንቴ የአርሶደር ቤተሰቡ በጥረት፤ በውጤማትና በአርያነት የሚጠቀስ ነው ብለዋል ።

ለነዋሪዎች ንፁህ የወተት ምርትን በማቅረብ የበለጠ በርትተው እንዲሰሩ የሙያና የቴክኒክ ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝም ገልፀዋል። አቶ ሰለሞን አክለውም የከተማ ግብርና ሥራ ተጭባጭ ውጤት እያመጣ ስለመሆኑ የሰገነት የወተት ማምረቻ ድርጅት ማሳያ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በአለኸኝ አዘነ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review