የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ጣፎ አደባባይ አካባባቢ ደንብ እንዲያስከብሩ ከተሰጣቸው ሀላፊነት ውጪ ስነ-ምግባር በጎደለው መልኩ ህገ ወጥ የጎዳና ነጋዴን በመደብደብና ንብረቱን በመበተን የስነ-ምግባር ጥፍት የፈፀሙ ባለሙያዎችን በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ማድረጉን ገለጸለ፡፡
ህብረተሰቡን በማክበር በታማኝነትና በቅንነት ደንብ እንዲያስከብሩ በተደጋጋሚ የሙያዊ ስነ-ምግባር ስልጠና መስጠቱን የገለጸው ባለስልጣኑ፣ የተሰጣቸውን ሀላፊነት በአግባቡ በማይወጡና ሙያዊ ስነ-ምግባር በጎደላቸው ባለሙያዎች ላይ የሚወስደን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል።
ባለስልጣኑ አከሎም፣ ጥፋቱን በፈፀሙ ባለሙያዎች ላይ መረጃውን በማጣራት እና በቁጥጥር ስር በማዋል ክስ እንዲመሠረትባቸው ማድረጉን ገልጿል።
ባለስልጣኑ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በላከው መረጃ እንደገለጸው፣ ህብረተሰቡ አንዳንድ ግድ የለሽ እና ስነ-ምግባር የጎደላቸው ባለሙያዎች ሲያጋጥሙት፣ በ9995 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጥም ጥሪውን አቅርቧል፡፡