በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የታጠቁ ኃይሎች የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ትጥቃቸውን ለሀገር መከላከያ ሰራዊት አስረክበዋል።
ታጣቂዎቹ በብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን በደብረብርሃን ጊዜያዊ የተሀድሶ ስልጠና ማዕከል አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና የመከላከያ ሰራዊት የጦር መኮንኖች እንዲሁም የዓለም አቀፍ ተቋማት ታዛቢዎች ተገኝተዋል።
በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች በግጭት የሚፈታ ጥያቄ አለመኖሩን ተገንዝበው መንግስትና ህዝብ የሰጣቸውን የሰላም አማራጭ እንዲቀበሉ ጥሪ ቀርቧል።
በካሳሁን አንዱአለም