የታጠቁ ኃይሎች የሰላም አማራጭን ተቀብለው ወደ ማህበረሰባቸው እንዲቀላቀሉ መንግስት በትኩረት እየሰራ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ

You are currently viewing የታጠቁ ኃይሎች የሰላም አማራጭን ተቀብለው ወደ ማህበረሰባቸው እንዲቀላቀሉ መንግስት በትኩረት እየሰራ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ

AMN – ነሐሴ 22/2017 ዓ.ም

መንግስት ከግማሽ መንገድ በላይ ተጉዞ የታጠቁ ኃይሎች የሰላም አማራጭን እንዲቀበሉ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ መቀጠሉን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚንስትር ዴኤታ አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ ተናገሩ።

የብሄራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን በአማራ ክልል ከ6ሺህ በላይ ለሚሆኑ የቀድሞ ታጣቂዎች በደብረ ብርሃን ፣ ኮምቦልቻ እና ጎንደር -ፀዳ ማዕከላት የተሀድሶ ስልጠና መሰጠት ጀምሯል።

በደብረብርሃን የተሀድሶ ስልጠና ማዕከል ተገኝተው ለቀድሞ ታጣቂዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት ሚንስትር ዴኤታው መንግስት የሰላም አማራጭን የመረጡ የቀድሞ ታጣቂዎችን ለማቋቋም የጀመረውን ተግባር አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

መንግስት ከህዝብ ጋር በመሆን ሰላምን ለማጽናት ሁሌም ዝግጁ መሆኑንም አቶ ተስፋሁን ተናግረዋል።

በካሳሁን አንዱአለም

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review