ፋብሪካዉ በ 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር በጀት ይገነባል
በ40 ወራት ዉስጥ ለማጠናቀቅ ይሰራል
ፋብሪካዉበዓመት ሦስት ሚሊየን ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ የማምረት አቅም አለዉ
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ የ40 በመቶ ድርሻ አለዉ
የዳንጎቴ ግሩፕ ደግሞ የ60 በመቶ ድርሻ ይኖረዋል
የፋብሪካዉ የማምረት አቅም በዘርፉ ከፍተኛ አምራች ከሆነችው ናይጄሪያ ጋር ተመሳሳይ ነዉ
ፋብሪካዉ ኢትዮጵያ የጀመረችውን የብልጽግና ጉዞ ከሚያረጋግጡ አንኳር ስትራቴጂክ ኢንቨስትመንቶች መካከል አንደኛው ነው
የኢትዮጵያን አርሶአደሮች የረጅም ጊዜ ጥያቄ የሚመልስ ነው
ፋብሪካዉን የሚገነቡት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ እና ዳንጎቴ ግሩፕ ናቸዉ
ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያ ያላትን የተፈጥሮ ነዳጅ በመጠቀም የነዳጅ ማስተላለፍያ መስመር ተገንብቶለት ወደ ስራ ይገባል
የዩሪያ ማዳበርያ አንደኛው ግብዓት የተፈጥሮ ነዳጅ ነው
ይህንን ነዳጅ ከካሉብና ሂላላ ሪዘርቭ በመውሰድ ወደ 109 ኪሎሜትር የነዳጅ ማስተላለፍያ መስመር ይገነባል
ይህ የነዳጅ ማስተላለፍያ መስመር ሶማሌ ክልል ጎዴ ድረስ ይደርሳል
ፋብሪካው የሚገነባዉ በጎዴ ነዉ
የተፈጥሮ ጋዙ ለሌሎች ግብዓት መሆን ይችላል
ከፋብሪካ በተጨማሪ በጎዴ የኢትዮጵያን የፔትሮኬሚካል ኢንዱስትሪ ለማቋቋም እቅድ ተይዟ