ከንቲባ አዳነች አቤቤ አዲስ አበባ በአለም አደባባይ ሌላኛዋ የኩራታችን ምንጭ ነች ሲሉ ገለጹ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ አዲስ አበባ በአለም አደባባይ ሌላኛዋ የኩራታችን ምንጭ ነች ሲሉ ገለጹ

AMN ነሃሴ 22/2017

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልዕክት ባለፉት የለዉጥ አመታት ከተማችን አዲስ አበባን በሁለንተናዊ መልኩ ለነዋሪዎቿ የተመቸች ፣ ለጎብኚዎቿ የተመረጠችና እንደ ስሟ ዉብ አበባ እናደርጋታለን ብለን ከነዋሪዎቻችን ጋር ሌት ተቀን የሰራናቸዉ ስራዎች ይኸዉ ዛሬ ፍሬ አፍርተዉ በአለም አደባባይ አሸናፊ እያደረጉን ይገኛል ።

በተለያዩ መወዳደሪያ መስፈርቶች እየመዘነ እዉቅና እና ደረጃ የሚሰጠዉ የብሉምበርግ ፍላንተሮፒስ ግብረ ሰናይ ድርጅት በከተማችን አዲስ አበባ የነዋሪዎቻችንን የአደጋ ተጋላጭነት ለመቀነስና ለመቆጣጠር በመንገድ ደህንነትና ፍጥነት ማስተዳደር ላይ በአጭር ጊዜ የሰራነዉን ስራና በተጨባጭ ያስመዘገብነዉን ዉጤት በመገምገም በአለም አቀፍ የከተምች የዘርፉ ዉድድር ላይ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ አድርጎናል ሲሉ ገልጸዋል።

ይህንን እዉቅናና ክብር የሰጠንን ብሉምበርግ ፍላንተሮፒስን በከተማ አስተዳደራችን ስም ከልብ እያመሰገንኩ በቀጣይም መዲናችንን በሁሉም መመዘኛዎች የተሻለች አለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንድትሆን የበለጠ መትጋታችን ይቀጥላል በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review