ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመደገፍ ወንጀል ላይ ተጨባጭ እርምጃ መውሰድ እንደሚገባ ተገለፀ

You are currently viewing ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመደገፍ ወንጀል ላይ ተጨባጭ እርምጃ መውሰድ እንደሚገባ ተገለፀ

AMN – ነሐሴ 23/2017 ዓ.ም

በቀጣናው ደህንነቱ የተጠበቀ የፋይናንስ ስርዓት ለመገንባት አገሮች ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመደገፍ ወንጀል ላይ ተጨባጭ እርምጃ መውሰድ እንዳለባቸው የምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ጸረ ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ቡድን ዋና ፀሐፊ ፋይክል ዚታ ገለጹ።

ኢትዮጵያ የምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ጸረ ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ቡድን 50ኛው የከፍተኛ ባለሙያዎች፣ 25ኛው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ እና ስምንተኛውን የመንግስትና የግሉ ዘርፍ የውይይት ፎረም እያስተናገደች ነው።

በዛሬው ዕለትም የምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ጸረ ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ቡድን 25ኛው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን መካሄድ ጀምሯል።

የምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ጸረ ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ቡድን ዋና ፀሐፊ ፋይክል ዚታ በዚህ ወቅት፣ የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ለምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ጸረ ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ቡድን ስብሰባ ላደረገልን የሞቀ አቀባበል እናመሰግናለን ብለዋል።

በቀጣናው ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መደገፍን ለመከላከል አገሮች የተጠናከረ እርምጃ መውሰድ እንደሚጠበቅባቸው መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ጸረ ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ቡድን ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርና ማጭበርበርን መከላከል የሚያስችል ትብብር መፍጠር ይገባል ብለዋል።

በቀጣናው የተጠናከረ የፋይናንስ ሥርዓት ለመገንባት በተቋማት መካከል ጠንካራ ትብብር መኖር እንዳለበትም አጽንኦት ሰጥተዋል።

የፋይናንስ ወንጀሎችን ለመከላከል በስብሰባው ላይ የሚተላለፉ ውሳኔዎችን ገቢራዊ ማድረግ እንደሚገባም ተናግረዋል።

የፋይናንስ ተቋማትን ደህንነት በማረጋገጥ የዜጎችን ዕምነት ማሳደግ እንደሚገባ በመግለፅ፤ ለዚህ ደግሞ አገሮች የህግ ማስከበርና የቁጥጥር ስርዓታቸውን ማጠናከር አለባቸው ብለዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review