አጠቃላዩ የኮሪደር ልማት አሠራር ለመጪው ጊዜ ታላቅ ተስፋ የሚሰጠን ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ

You are currently viewing አጠቃላዩ የኮሪደር ልማት አሠራር ለመጪው ጊዜ ታላቅ ተስፋ የሚሰጠን ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ

AMN – ነሐሴ 24/2017 ዓ.ም

አጠቃላዩ የኮሪደር ልማት አሠራር ለመጪው ጊዜ ታላቅ ተስፋ የሚሰጠን ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልእክት በመጀመሪያው ምዕራፍ በአራት ኮሪደሮች ጀምረን በሁለተኛው ምዕራፍ በስምንት ኮሪደሮች ቀጥለናል ብለዋል። የተጠናቀቀውን እና 12.74 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውን ከአዲስ ኮንቬንሽን መዐከል-ጎሮ-ቪአይፒ ኤርፖርት ኮሪደር ዛሬ ተመልክተናል ብለዋል።

በኮሪደሩ 29 ኪሎሜትር የእግረኛ መንገድ እና 15.27 ኪሎሜትር የብስክሌት መጋለቢያ መሰራቱን የገለፁ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይኽ የኮሪደር ሥራ ሰፋፊ የተሽከርካሪ መንገዶችን፣ ከጎሮ እስከ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ አዲስ መንገድ እንዲሁም በአካባቢው ሰፊ የወንዝ ልማትን ያካተተ ነው ብለዋል። ሰባት የስፖርት ማዕከላት፣ የመኪና ማቆሚያዎች፣ የታክሲ እና አውቶቡስ መናኸሪያዎች፣ ካፌዎች፣ የሕዝብ መጸዳጃዎች እና ሌሎች አገልግሎት መስጫዎች የተካተቱበት እንደሆነ ገልፀዋል።

እነኚህ ግንባታዎች ሥራ ፈጥረዋል፣ መገናኛ እና መዳረሻዎችን አስፋፍተዋል፣ የከተማዋን መሠረተ ልማት አጠናክረዋል ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሁሉም መስክ ኢትዮጵያ መበርታቷን ቀጥላለች። ወደ ብልጽግና የምናደርገው ጉዞ አይደናቀፍም። አይቆምም። የእነኚህ ሥራዎች ስኬት ይኽንን ያስቻለውን የተለወጠ ርዕይ እና የሥራ ባሕል ያንፀባርቃል ብለዋል። እስከአሁን የከተማዋ ግማሽ ያህል የተለወጠ ሲሆን የበለጠ ለማሻሻል የምንተጋባቸው ከባቢዎች አሁንም ይቀራሉ ብለዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review